Continental Drift

ከዕዳ ወደ ፋይናንስ ሉዓላዊነት፡ የአፍሪካ አዲስ የካፒታል ስትራቴጂ

1 h 0 min · I går
episode ከዕዳ ወደ ፋይናንስ ሉዓላዊነት፡ የአፍሪካ አዲስ የካፒታል ስትራቴጂ cover

Description

ኢትዮጵያ ወደ ዘመናዊ የካፒታል ገበያ ሥርዓት የምታደርገው ሽግግር ከኢኮኖሚ ማሻሻያ ባለፈ፣ የሀገሪቱን የፋይናንስ ተቋማት አቅም እና ቁጥጥር የሚፈትን ትልቅ እርምጃ ነው። ይህ ለውጥ ግልጽነትን፣ ጠንካራ የሂሳብ አያያዝን እና ተወዳዳሪ የሆኑ የሀገር ውስጥ የኢንቨስትመንት ባንኮችን መኖር የግድ ይላል። "ገበያው በተለያዩ መንገዶች ዝግጁ መሆን እንዳለበት እናውቃለን። አንደኛው ነገር ግልጽነት እና ተገቢ የሆነ የፋይናንስ መዝገብ አያያዝ አስፈላጊነት ነው። በዚህ ረገድ እንደ IFRS ያሉ የሂሳብ አያያዝ ሥርዓቶች በተለያዩ ተቋማት ውስጥ ተግባራዊ መደረጋቸው ትልቅ እርምጃ ነው። ከዚህ በተጨማሪም የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ከ50 በላይ ባለአክሲዮኖች ያሏቸው አክሲዮን ማኅበራት በባለሥልጣኑ ዘንድ መመዝገብ እንዳለባቸው በግልጽ አመልክቷል።" ሲሉ የአዋሽ ኢንቨስትመንት ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አንዱዓለም ኃይሉ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡  በዛሬው የኮንቲነንታል ድሪፍት ዝግጅታችን፣ የኢትዮጵያን የካፒታል ገበያ ዝግጁነት እና የአህጉሪቱን የሉዓላዊ ዕዳ ፈተናዎች በሦስት አቅጣጫዎች እንፈትሻለን። ለዚህም ከአዋሽ ኢንቨስትመንት ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አንዱዓለም ኃይሉ(ዶ/ር) ፣ ከኤፍ ኤስ ዲ አፍሪካ የሉዓላዊ ዕዳ አማካሪ ሄንሪ ኪየሬሜ እና ከተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን (UNECA) የፋይናንስ ዘርፍ ኃላፊ ሶንያ ኢሶፕማድዬ ጋር ቆይታ አድርገናል።

Comments

0

Be the first to comment

Sign up now and become a member of the Continental Drift community!

Get Started

1 month for 9 kr.

Then 99 kr. / month · Cancel anytime.

  • Podcasts kun på Podimo
  • 20 lydbogstimer pr. måned
  • Gratis podcasts

All episodes

22 episodes

episode ከዕዳ ወደ ፋይናንስ ሉዓላዊነት፡ የአፍሪካ አዲስ የካፒታል ስትራቴጂ artwork

ከዕዳ ወደ ፋይናንስ ሉዓላዊነት፡ የአፍሪካ አዲስ የካፒታል ስትራቴጂ

ኢትዮጵያ ወደ ዘመናዊ የካፒታል ገበያ ሥርዓት የምታደርገው ሽግግር ከኢኮኖሚ ማሻሻያ ባለፈ፣ የሀገሪቱን የፋይናንስ ተቋማት አቅም እና ቁጥጥር የሚፈትን ትልቅ እርምጃ ነው። ይህ ለውጥ ግልጽነትን፣ ጠንካራ የሂሳብ አያያዝን እና ተወዳዳሪ የሆኑ የሀገር ውስጥ የኢንቨስትመንት ባንኮችን መኖር የግድ ይላል። "ገበያው በተለያዩ መንገዶች ዝግጁ መሆን እንዳለበት እናውቃለን። አንደኛው ነገር ግልጽነት እና ተገቢ የሆነ የፋይናንስ መዝገብ አያያዝ አስፈላጊነት ነው። በዚህ ረገድ እንደ IFRS ያሉ የሂሳብ አያያዝ ሥርዓቶች በተለያዩ ተቋማት ውስጥ ተግባራዊ መደረጋቸው ትልቅ እርምጃ ነው። ከዚህ በተጨማሪም የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ከ50 በላይ ባለአክሲዮኖች ያሏቸው አክሲዮን ማኅበራት በባለሥልጣኑ ዘንድ መመዝገብ እንዳለባቸው በግልጽ አመልክቷል።" ሲሉ የአዋሽ ኢንቨስትመንት ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አንዱዓለም ኃይሉ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡  በዛሬው የኮንቲነንታል ድሪፍት ዝግጅታችን፣ የኢትዮጵያን የካፒታል ገበያ ዝግጁነት እና የአህጉሪቱን የሉዓላዊ ዕዳ ፈተናዎች በሦስት አቅጣጫዎች እንፈትሻለን። ለዚህም ከአዋሽ ኢንቨስትመንት ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አንዱዓለም ኃይሉ(ዶ/ር) ፣ ከኤፍ ኤስ ዲ አፍሪካ የሉዓላዊ ዕዳ አማካሪ ሄንሪ ኪየሬሜ እና ከተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን (UNECA) የፋይናንስ ዘርፍ ኃላፊ ሶንያ ኢሶፕማድዬ ጋር ቆይታ አድርገናል።

Yesterday1 h 0 min
episode ከምዕራባውያን ተጽዕኖ ባሻገር፦ የፑቲን እና ሺ ጂንፒንግ ግንኙነት የአፍሪካን ሉዓላዊነት እንዴት ይቀርጻል? artwork

ከምዕራባውያን ተጽዕኖ ባሻገር፦ የፑቲን እና ሺ ጂንፒንግ ግንኙነት የአፍሪካን ሉዓላዊነት እንዴት ይቀርጻል?

"የቭላድሚር ፑቲን የቻይና ጉብኝት የዓለም ሥርዓት ከአንድ ዋልታ ወደ ባለብዙ-ዋልታ እየተቀየረ መሆኑን ካሳዩ ግልጽ ማረጋገጫዎች አንዱ ነው። ይህ ጉብኝት የምዕራባውያን አገራት በዓለም መድረክ ላይ የነበራቸው የበላይነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ መምጣቱን የሚያሳይ ግልጽ ምልክት ነው" ሲሉ ሙሉዓለም ኃይለማርያም በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ በዛሬው የኮንቲነንታል ድሪፍት ዝግጅታችን ሁለት አበይት ጉዳዮችን ይዘንላችሁ ቀርበናል ፤ የፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የቤጂንግ ጉብኝት እና ለአፍሪካ የሉዓላዊነት ጉዞ የሚኖረው ስትራቴጂካዊ ትርጉም ከዓለም አቀፍ ግንኙነት ምሁሩ ሙሉዓለም ኃይለማርያም ጋር ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ወደ መካከለኛው ምስራቅ የምታደርገውን የስጋ ኤክስፖርት በከፍተኛ አቅም ዳግም መጀመሯ እና የተከፈተው አዲስ የ"ግመል ስጋ" ገበያ ከአላና ግሩፕ ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኸሊፋ ሁሴን ጋር ተወያይተዋል።  ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ፡

20. maj 20261 h 0 min
episode የአፍሪካን የኢኮኖሚ አእምሮ ማን ይገነባዋል? ዕውቀት፣ ስፖርት እና አዲሱ የሉዓላዊነት ትግል artwork

የአፍሪካን የኢኮኖሚ አእምሮ ማን ይገነባዋል? ዕውቀት፣ ስፖርት እና አዲሱ የሉዓላዊነት ትግል

የአፍሪካ ሉዓላዊነት ጥያቄ ከማዕድን እና ከንግድ ኮሪደሮች ባለፈ፣ አህጉሪቱን የሚያስተዳድሩ መሪዎች በሚቀረጹበት የዕውቀት ሥርዓት ላይ ያተኩራል። በሌላ በኩል ደግሞ አዲስ አበባ የመጀመሪያውን አህጉራዊ የተራራ ብስክሌት ውድድር በማስተናገድ፣ ከተማን እንደ ዲፕሎማሲ እና የ'ሶፍት ፓወርን' መድረክነት እየተጠቀመችበት ትገኛለች። "አፍሪካውያን የራሳቸውን ሥርዓተ-ትምህርት ማዘጋጀት አለባቸው። ይህም በጣም አስፈላጊ ነው። ሌላው ችግር በመካከላችን ጠንካራ አህጉራዊ ግንኙነት የለንም። ስለዚህ ይህንን ግንኙነት መገንባት አለብን። ይህ ጉባኤ የአፍሪካ ቢዝነስ ትምህርት ቤቶች በራሳቸው ችግሮች ላይ ተመሥርተው በጋራ እንዲሠሩ በማድረግ ረገድ ትልቅ ፋይዳ ይኖረዋል።" ሲሉ ደሳለኝ መኩሪያ ንጉሤ፣ የክቡር ኮሌጅ ፕሬዝዳንት ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ በዛሬው የኮንቲነንታል ድሪፍት ዝግጅታችን፣ አፍሪካ የራሷን ተቋማት በራሷ ፍላጎት ላይ ተመሥርታ የመገንባት ስትራቴጂን ከሁለት እንግዶች ጋር እንፈትሻለን፦ ከክቡር ኮሌጅ ፕሬዝዳንት ደሳለኝ መኩሪያ ንጉሤ ጋር ስለ ቢዝነስ ትምህርት፣ አመራር እና ስለ ዕውቀት ሉዓላዊነት፤ ከኢትዮጵያ ብስክሌት ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ወዲሙ ኃይሌ ጋር ስለ ከተማ ስፖርት ዲፕሎማሲ እና ስለ አዲስ አበባ ገጽታ ግንባታ እንወያያለን። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በአእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ ፡

18. maj 20261 h 0 min
episode "ያመለጡ አጋጣሚዎች እና የደቀኑብን ስጋቶች"፦ የመካከለኛው ምስራቅ ቀውስ ለአፍሪካ የምግብ ሉዓላዊነት የመጨረሻው ማስጠንቀቂያ artwork

"ያመለጡ አጋጣሚዎች እና የደቀኑብን ስጋቶች"፦ የመካከለኛው ምስራቅ ቀውስ ለአፍሪካ የምግብ ሉዓላዊነት የመጨረሻው ማስጠንቀቂያ

በዓለም አቀፍ ደረጃ እየታየ ያለው አለመረጋጋት—ከአሜሪካ እና ኢራን ፍጥጫ እስከ ቀይ ባሕር የጸጥታ ስጋት በአፍሪካውያን ማዕድ ላይ ቀጥተኛ ተጽዕኖ እያሳደረ ይገኛል። እንዴት ? "እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ታዳጊ ሀገራት በከፍተኛ ሁኔታ በዕርዳታ ላይ ጥገኛ ናቸው። [...] ይህ ለእኛ ሌላ የዝግጅት ጊዜ ሊሰጠን ይገባ ነበር። እውነቱን ለመናገር፣ የዓለም ሥርዓት ወዴት እየሄደ እንደሆነ በጥንቃቄ ብንከታተል ኖሮ፣ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን እንደ ጥሩ አጋጣሚ ልንጠቀምበት እንችል ነበር።" — ሲሉ አሻግሬ ዘውዱ (ዶ/ር) በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተፈጥሮ ሳይንስ ኮሌጅ የምግብና የሥነ ምግብ ማዕከል ተባባሪ ፕሮፌሰር ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬው የኮንቲነንታል ድሪፍት ዝግጅታችን፤ ከመካከለኛው ምስራቅ ቀውስ ተጽዕኖ በመውጣት የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ከሥነ-ምግብ ባለሙያና ተመራማሪው አሻግሬ ዘውዱ (ዶ/ር) ጋር ተወያይተናል። በሁለተኛው ክፍል ደግሞ የአፍሪካን መጻኢ ዕድል በመቅረጽ ረገድ ያለውን የወጣቶች ሚና እንቃኛለን። ለዚህም የኢንተርናሽናል ዩዝ ኮኔክት (IYC) ዳይሬክተር ዳንኤል ዚንያማ እና የፓን-አፍሪካኒዝም ተሟጋቿ ኒያሻ አዶር ጋዚምቢ በእንግድነት ቀርበዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ ፡

6. apr. 20261 h 0 min
episode የእስራኤል እና አሜሪካ ጥቃት በኢራን ላይ፡- ለአፍሪካ የጂኦፖለቲካ ትምህርቶች artwork

የእስራኤል እና አሜሪካ ጥቃት በኢራን ላይ፡- ለአፍሪካ የጂኦፖለቲካ ትምህርቶች

በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ውጥረት የዓለምን የኢነርጂ ፍሰት እና ዲፕሎማሲያዊ አሰላለፍ እየቀየረ ነው ። በተለይም በሆርሙዝ የባህር በር ላይ የሚፈጠር አለመረጋጋት በአፍሪካ የኑሮ ውድነት ላይ ቀጥተኛ ተጽዕኖ አለው ። "አፍሪካ አሁን ማድረግ የምትችለው ነገር ተጋላጭነቷን እና ጥገኝነቷን ለመቀነስ መሞከር ነው። ለዚህም ኢትዮጵያ በጣም ጥሩ ምሳሌ ናት። ባለፉት ጥቂት አስርት ዓመታት ውስጥ ኢትዮጵያ በአንድ የውጭ የገንዘብ ድጋፍ ሰጪ ላይ ብቻ ጥገኛ እንዳትሆን የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ምንጮቿን በማባዛት ረገድ የተሳካ ስራ ሰርታለች።" ሲሉ የምጣኔ ሀብት እና የፖለቲካ ኢኮኖሚ ባለሙያ ፕሮፌሰር ማቲው ማካርትኒ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬው የኮንቲነንታል ድሪፍት ዝግጅታችን፣ በመካከለኛው ምስራቅ የተቀሰቀሰው ግጭት በኢትዮጵያ፣ በአፍሪካ እና በአጠቃላይ በደቡባዊው የዓለም ክፍል ላይ የሚያሳድረውን ዘለቄታዊ ተጽዕኖ በሶስት የተለያዩ አቅጣጫዎች እንቃኛለን ። ለዚህም ከኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲው ፕሮፌሰር ማቲው ማካርትኒ፣ በዱባይ ይኖር ከነበረው ተማሪ አናኦል ሚካኤል እና ከስትራቴጂክ ተንታኙ ሚካኤል ገዛኸኝ ጋር ቆይታ አድርገናል።  ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ ፡

26. mar. 20261 h 0 min