Kansikuva näyttelystä Continental Drift

Continental Drift

Podcast by Eden Teshome

englanti

Uutiset & politiikka

Rajoitettu tarjous

3 kuukautta hintaan 3,99 €

Sitten 7,99 € / kuukausiPeru milloin tahansa.

  • Podimon podcastit
  • Lataa offline-käyttöön
Aloita nyt

Lisää Continental Drift

''Continental Drift' is a program tracking the tectonic changes reshaping Africa and redefining the Global South's role in the world. The show explores how policies, markets, and innovation intersect with everyday lives, offering fact-based insights and authentic African perspectives. Through interviews, explainers, and ground-level reporting, the program connects big shifts to real impact making complex issues clear, relevant, and accessible.' is a program tracking the tectonic changes reshaping Africa and redefining the Global South's role in the world. The show explores how policies, markets, and innovation intersect with everyday lives, offering fact-based insights and authentic African perspectives. Through interviews, explainers, and ground-level reporting, the program connects big shifts to real impact making complex issues clear, relevant, and accessible.

Kaikki jaksot

21 jaksot

jakson ከምዕራባውያን ተጽዕኖ ባሻገር፦ የፑቲን እና ሺ ጂንፒንግ ግንኙነት የአፍሪካን ሉዓላዊነት እንዴት ይቀርጻል? kansikuva

ከምዕራባውያን ተጽዕኖ ባሻገር፦ የፑቲን እና ሺ ጂንፒንግ ግንኙነት የአፍሪካን ሉዓላዊነት እንዴት ይቀርጻል?

"የቭላድሚር ፑቲን የቻይና ጉብኝት የዓለም ሥርዓት ከአንድ ዋልታ ወደ ባለብዙ-ዋልታ እየተቀየረ መሆኑን ካሳዩ ግልጽ ማረጋገጫዎች አንዱ ነው። ይህ ጉብኝት የምዕራባውያን አገራት በዓለም መድረክ ላይ የነበራቸው የበላይነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ መምጣቱን የሚያሳይ ግልጽ ምልክት ነው" ሲሉ ሙሉዓለም ኃይለማርያም በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ በዛሬው የኮንቲነንታል ድሪፍት ዝግጅታችን ሁለት አበይት ጉዳዮችን ይዘንላችሁ ቀርበናል ፤ የፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የቤጂንግ ጉብኝት እና ለአፍሪካ የሉዓላዊነት ጉዞ የሚኖረው ስትራቴጂካዊ ትርጉም ከዓለም አቀፍ ግንኙነት ምሁሩ ሙሉዓለም ኃይለማርያም ጋር ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ወደ መካከለኛው ምስራቅ የምታደርገውን የስጋ ኤክስፖርት በከፍተኛ አቅም ዳግም መጀመሯ እና የተከፈተው አዲስ የ"ግመል ስጋ" ገበያ ከአላና ግሩፕ ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኸሊፋ ሁሴን ጋር ተወያይተዋል።  ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ፡

20. touko 2026 - 1 h 0 min
jakson የአፍሪካን የኢኮኖሚ አእምሮ ማን ይገነባዋል? ዕውቀት፣ ስፖርት እና አዲሱ የሉዓላዊነት ትግል kansikuva

የአፍሪካን የኢኮኖሚ አእምሮ ማን ይገነባዋል? ዕውቀት፣ ስፖርት እና አዲሱ የሉዓላዊነት ትግል

የአፍሪካ ሉዓላዊነት ጥያቄ ከማዕድን እና ከንግድ ኮሪደሮች ባለፈ፣ አህጉሪቱን የሚያስተዳድሩ መሪዎች በሚቀረጹበት የዕውቀት ሥርዓት ላይ ያተኩራል። በሌላ በኩል ደግሞ አዲስ አበባ የመጀመሪያውን አህጉራዊ የተራራ ብስክሌት ውድድር በማስተናገድ፣ ከተማን እንደ ዲፕሎማሲ እና የ'ሶፍት ፓወርን' መድረክነት እየተጠቀመችበት ትገኛለች። "አፍሪካውያን የራሳቸውን ሥርዓተ-ትምህርት ማዘጋጀት አለባቸው። ይህም በጣም አስፈላጊ ነው። ሌላው ችግር በመካከላችን ጠንካራ አህጉራዊ ግንኙነት የለንም። ስለዚህ ይህንን ግንኙነት መገንባት አለብን። ይህ ጉባኤ የአፍሪካ ቢዝነስ ትምህርት ቤቶች በራሳቸው ችግሮች ላይ ተመሥርተው በጋራ እንዲሠሩ በማድረግ ረገድ ትልቅ ፋይዳ ይኖረዋል።" ሲሉ ደሳለኝ መኩሪያ ንጉሤ፣ የክቡር ኮሌጅ ፕሬዝዳንት ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ በዛሬው የኮንቲነንታል ድሪፍት ዝግጅታችን፣ አፍሪካ የራሷን ተቋማት በራሷ ፍላጎት ላይ ተመሥርታ የመገንባት ስትራቴጂን ከሁለት እንግዶች ጋር እንፈትሻለን፦ ከክቡር ኮሌጅ ፕሬዝዳንት ደሳለኝ መኩሪያ ንጉሤ ጋር ስለ ቢዝነስ ትምህርት፣ አመራር እና ስለ ዕውቀት ሉዓላዊነት፤ ከኢትዮጵያ ብስክሌት ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ወዲሙ ኃይሌ ጋር ስለ ከተማ ስፖርት ዲፕሎማሲ እና ስለ አዲስ አበባ ገጽታ ግንባታ እንወያያለን። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በአእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ ፡

18. touko 2026 - 1 h 0 min
jakson "ያመለጡ አጋጣሚዎች እና የደቀኑብን ስጋቶች"፦ የመካከለኛው ምስራቅ ቀውስ ለአፍሪካ የምግብ ሉዓላዊነት የመጨረሻው ማስጠንቀቂያ kansikuva

"ያመለጡ አጋጣሚዎች እና የደቀኑብን ስጋቶች"፦ የመካከለኛው ምስራቅ ቀውስ ለአፍሪካ የምግብ ሉዓላዊነት የመጨረሻው ማስጠንቀቂያ

በዓለም አቀፍ ደረጃ እየታየ ያለው አለመረጋጋት—ከአሜሪካ እና ኢራን ፍጥጫ እስከ ቀይ ባሕር የጸጥታ ስጋት በአፍሪካውያን ማዕድ ላይ ቀጥተኛ ተጽዕኖ እያሳደረ ይገኛል። እንዴት ? "እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ታዳጊ ሀገራት በከፍተኛ ሁኔታ በዕርዳታ ላይ ጥገኛ ናቸው። [...] ይህ ለእኛ ሌላ የዝግጅት ጊዜ ሊሰጠን ይገባ ነበር። እውነቱን ለመናገር፣ የዓለም ሥርዓት ወዴት እየሄደ እንደሆነ በጥንቃቄ ብንከታተል ኖሮ፣ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን እንደ ጥሩ አጋጣሚ ልንጠቀምበት እንችል ነበር።" — ሲሉ አሻግሬ ዘውዱ (ዶ/ር) በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተፈጥሮ ሳይንስ ኮሌጅ የምግብና የሥነ ምግብ ማዕከል ተባባሪ ፕሮፌሰር ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬው የኮንቲነንታል ድሪፍት ዝግጅታችን፤ ከመካከለኛው ምስራቅ ቀውስ ተጽዕኖ በመውጣት የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ከሥነ-ምግብ ባለሙያና ተመራማሪው አሻግሬ ዘውዱ (ዶ/ር) ጋር ተወያይተናል። በሁለተኛው ክፍል ደግሞ የአፍሪካን መጻኢ ዕድል በመቅረጽ ረገድ ያለውን የወጣቶች ሚና እንቃኛለን። ለዚህም የኢንተርናሽናል ዩዝ ኮኔክት (IYC) ዳይሬክተር ዳንኤል ዚንያማ እና የፓን-አፍሪካኒዝም ተሟጋቿ ኒያሻ አዶር ጋዚምቢ በእንግድነት ቀርበዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ ፡

6. huhti 2026 - 1 h 0 min
jakson የእስራኤል እና አሜሪካ ጥቃት በኢራን ላይ፡- ለአፍሪካ የጂኦፖለቲካ ትምህርቶች kansikuva

የእስራኤል እና አሜሪካ ጥቃት በኢራን ላይ፡- ለአፍሪካ የጂኦፖለቲካ ትምህርቶች

በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ውጥረት የዓለምን የኢነርጂ ፍሰት እና ዲፕሎማሲያዊ አሰላለፍ እየቀየረ ነው ። በተለይም በሆርሙዝ የባህር በር ላይ የሚፈጠር አለመረጋጋት በአፍሪካ የኑሮ ውድነት ላይ ቀጥተኛ ተጽዕኖ አለው ። "አፍሪካ አሁን ማድረግ የምትችለው ነገር ተጋላጭነቷን እና ጥገኝነቷን ለመቀነስ መሞከር ነው። ለዚህም ኢትዮጵያ በጣም ጥሩ ምሳሌ ናት። ባለፉት ጥቂት አስርት ዓመታት ውስጥ ኢትዮጵያ በአንድ የውጭ የገንዘብ ድጋፍ ሰጪ ላይ ብቻ ጥገኛ እንዳትሆን የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ምንጮቿን በማባዛት ረገድ የተሳካ ስራ ሰርታለች።" ሲሉ የምጣኔ ሀብት እና የፖለቲካ ኢኮኖሚ ባለሙያ ፕሮፌሰር ማቲው ማካርትኒ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬው የኮንቲነንታል ድሪፍት ዝግጅታችን፣ በመካከለኛው ምስራቅ የተቀሰቀሰው ግጭት በኢትዮጵያ፣ በአፍሪካ እና በአጠቃላይ በደቡባዊው የዓለም ክፍል ላይ የሚያሳድረውን ዘለቄታዊ ተጽዕኖ በሶስት የተለያዩ አቅጣጫዎች እንቃኛለን ። ለዚህም ከኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲው ፕሮፌሰር ማቲው ማካርትኒ፣ በዱባይ ይኖር ከነበረው ተማሪ አናኦል ሚካኤል እና ከስትራቴጂክ ተንታኙ ሚካኤል ገዛኸኝ ጋር ቆይታ አድርገናል።  ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ ፡

26. maalis 2026 - 1 h 0 min
jakson የባህረ ሰላጤው የኢነርጂ ቀውስ እና የአፍሪካ ኢኮኖሚያዊ ተጋላጭነት kansikuva

የባህረ ሰላጤው የኢነርጂ ቀውስ እና የአፍሪካ ኢኮኖሚያዊ ተጋላጭነት

በመካከለኛው ምስራቅ የሚከሰት ግጭት እንዴት በአፍሪካውያን የዕለት ተዕለት ኑሮ፣ በትራንስፖርት እና በምግብ ዋጋ ላይ ቀጥተኛ ጫና ይፈጥራል? የዓለም የነዳጅ ገበያ መናጋት አፍሪካ የራሷን የኢነርጂ መሠረተ ልማት እንድትገነባ እና በውጭ ገበያ ላይ ያላትን ጥገኝነት እንድትቀንስ የማንቂያ ደወል ሊሆን ይችላል? "በዓለም አቀፍ የነዳጅ ዋጋ ላይ የሚታየው ከፍተኛ መዋዠቅ፣ በተለይም እንደ አፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ባሉ ማዕቀፎች ውስጥ ጠንካራ የአህጉር አቀፍ የኢነርጂ ትብብር እንዲኖር እንደ ማነቃቂያ ሊያገለግል ይችላል። እዚህ ላይ አንድ ዋና ነጥብ መጥቀስ እንችላለን፤ ምክንያቱም ከውጭ በሚገቡ ምርቶች ላይ ያለውን ጥገኝነት መቀነስ አስፈላጊ ነው፤ ረጅም ጊዜ የሚወስዱ ዓለም አቀፍ የዋጋ ድንጋጤዎች በእነዚህ ምርቶች ላይ ጥገኛ የሆኑ ሀገራትን ተጋላጭነት ጎልቶ እንዲወጣ ያደርጋሉ። በመሆኑም በጋራ ቀጠናዊ የነዳጅ ማጣሪያ ተቋማት እና ድንበር ተሻጋሪ የኤሌክትሪክ ትስስር አማካኝነት ቀጠናዊ የኢነርጂ ትብብርን ማጠናከር ይገባል።" ሲሉ በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የማኅበረ-ኢኮኖሚ ተመራማሪው መሐመድ ኢብራሂም ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።  በዛሬው የኮንቲነንታል ድሪፍት ዝግጅታችን፣ በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ውጥረት በዓለም የነዳጅ አቅርቦት እና በአፍሪካ ኢኮኖሚ ላይ የሚያሳድረውን ተጽዕኖ ከአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የማኅበረ-ኢኮኖሚ ተመራማሪው መሐመድ ኢብራሂም ጋር በጥልቀት እንመረምራለን። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ ፡

16. maalis 2026 - 1 h 0 min
Loistava design ja vihdoin on helppo löytää podcasteja, joista oikeasti tykkää
Loistava design ja vihdoin on helppo löytää podcasteja, joista oikeasti tykkää
Kiva sovellus podcastien kuunteluun, ja sisältö on monipuolista ja kiinnostavaa
Todella kiva äppi, helppo käyttää ja paljon podcasteja, joita en tiennyt ennestään.

Valitse tilauksesi

Suosituimmat

Rajoitettu tarjous

Premium

  • Podimon podcastit

  • Ei mainoksia Podimon podcasteissa

  • Peru milloin tahansa

3 kuukautta hintaan 3,99 €
Sitten 7,99 € / kuukausi

Aloita nyt

Premium

20 tuntia äänikirjoja

  • Podimon podcastit

  • Ei mainoksia Podimon podcasteissa

  • Peru milloin tahansa

30 vrk ilmainen kokeilu
Sitten 9,99 € / kuukausi

Aloita maksutta

Premium

100 tuntia äänikirjoja

  • Podimon podcastit

  • Ei mainoksia Podimon podcasteissa

  • Peru milloin tahansa

30 vrk ilmainen kokeilu
Sitten 19,99 € / kuukausi

Aloita maksutta

Vain Podimossa

Suosittuja äänikirjoja

Aloita nyt

3 kuukautta hintaan 3,99 €. Sitten 7,99 € / kuukausi. Peru milloin tahansa.