Continental Drift
ኢትዮጵያ ወደ ዘመናዊ የካፒታል ገበያ ሥርዓት የምታደርገው ሽግግር ከኢኮኖሚ ማሻሻያ ባለፈ፣ የሀገሪቱን የፋይናንስ ተቋማት አቅም እና ቁጥጥር የሚፈትን ትልቅ እርምጃ ነው። ይህ ለውጥ ግልጽነትን፣ ጠንካራ የሂሳብ አያያዝን እና ተወዳዳሪ የሆኑ የሀገር ውስጥ የኢንቨስትመንት ባንኮችን መኖር የግድ ይላል። "ገበያው በተለያዩ መንገዶች ዝግጁ መሆን እንዳለበት እናውቃለን። አንደኛው ነገር ግልጽነት እና ተገቢ የሆነ የፋይናንስ መዝገብ አያያዝ አስፈላጊነት ነው። በዚህ ረገድ እንደ IFRS ያሉ የሂሳብ አያያዝ ሥርዓቶች በተለያዩ ተቋማት ውስጥ ተግባራዊ መደረጋቸው ትልቅ እርምጃ ነው። ከዚህ በተጨማሪም የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ከ50 በላይ ባለአክሲዮኖች ያሏቸው አክሲዮን ማኅበራት በባለሥልጣኑ ዘንድ መመዝገብ እንዳለባቸው በግልጽ አመልክቷል።" ሲሉ የአዋሽ ኢንቨስትመንት ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አንዱዓለም ኃይሉ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ በዛሬው የኮንቲነንታል ድሪፍት ዝግጅታችን፣ የኢትዮጵያን የካፒታል ገበያ ዝግጁነት እና የአህጉሪቱን የሉዓላዊ ዕዳ ፈተናዎች በሦስት አቅጣጫዎች እንፈትሻለን። ለዚህም ከአዋሽ ኢንቨስትመንት ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አንዱዓለም ኃይሉ(ዶ/ር) ፣ ከኤፍ ኤስ ዲ አፍሪካ የሉዓላዊ ዕዳ አማካሪ ሄንሪ ኪየሬሜ እና ከተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን (UNECA) የፋይናንስ ዘርፍ ኃላፊ ሶንያ ኢሶፕማድዬ ጋር ቆይታ አድርገናል።
22 afleveringen
Reacties
0Wees de eerste die een reactie plaatst
Meld je nu aan en word lid van de Continental Drift community!