Drum of Changes
"ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት (ICC) ወደ ሕጋዊ ማጭበርበሪያነት ተቀይሯል፤ ተቋሙ ከአሁን በኋላ የፍትህ አደባባይ ሳይሆን፣ የአሜሪካን የበላይነት ለማስጠበቅና የአፍሪካ መሪዎችን ለብቻቸው ነጥሎ ለማጥቃት በስልት የሚዘወር ታዛዥ መሣሪያ ሆኗል፤ ይህ ሁሉ በሚሆንበት ጊዜ ግን የምዕራባውያን የበላይነት አርክቴክቶች እጃቸው አይነካም።" ሲሉ —በዓለም አቀፍ ግንኙነት የዘርፍ ምሁር — ፕሮፌሰር ኤሊ ጂርጂ ኤልያስ፣ በሊባኖስ የዩኒቨርሲቲ በዓለም አቀፍ ግንኙነትና ስትራቴጂ ጥናት ልዩ ባለሙያና መምህር ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬው የድረም ኦፍ ጄንጅስ ዝግጅታችን የሚከተሉትን ሶስት ዋና ዋና ጉዳዮች ከአንግዶቻችን ጋር በዝርዝር እንቃኛለን፦ • ዓለም አቀፍ ፍትህ ወይንስ የምዕራባውያን የበላይነት መጠቀሚያ? — ከዓለም አቀፍ ግንኙነት ምሁሩ ፕሮፌሰር ኤሊ ጂርጂ ኤልያስ ጋር። • የአፍሪካ ከተሞች የወደፊት ዕጣ ፈንታና የቤት ልማት ፈተናዎች — ከዩኤን-ሀቢታት (UN-Habitat) ዋና ዳይሬክተር አናክላውዲያ ሮስባክ ጋር። • የመድኃኒት ዋስትና እና የአፍሪካ ሉዓላዊነት — ከኢትዮጵያ መድኃኒትና የሕክምና መገልገያ አቅራቢዎች ማኅበር ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዳንኤል ዋክቶሌ ጋር። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:
33 episoder
Kommentarer
0Vær den første til at kommentere
Tilmeld dig nu og bliv en del af Drum of Changes-fællesskabet!