Drum of Changes

85ኛው የአርበኞች ድል በዓል፡- የሊግ ኦፍ ኔሽንስ ክህደት እና የኢትዮጵያ ጽናት

1 h 0 min · 5 de may de 2026
Portada del episodio 85ኛው የአርበኞች ድል በዓል፡- የሊግ ኦፍ ኔሽንስ ክህደት እና የኢትዮጵያ ጽናት

Descripción

ኢትዮጵያ 85ኛውን የአርበኞች ድል በዓል ዛሬ ሚያዚያ 27 ቀን ፣ 2018 ዓ.ም አክብራለች፡፡ ''በወቅቱ የአውሮፓ ኃያላን ከአንደኛው የዓለም ጦርነት ያጡትን ካፒታልና ሀብት መልሶ ለማግኘት አፍሪካን እንደ ግብዓትና የጉልበት ምንጭ ተጠቅመዋል። ጣሊያን በ1889 በዓድዋ ጦርነት የደረሰባትን ሽንፈት ለመቀልበስና የኢንዱስትሪ አብዮቷን ለመደገፍ ኢትዮጵያን በሙሉ አቅሟ ለመቆጣጠር መጣች። [...] የሊግ ኦፍ ኔሽንስ በኢትዮጵያ ላይ የተደቀነውን ወረራ ማስቆም አልቻለም። እንዲያውም የድርጅቱ አባል የሆኑት እንደ ብሪታንያ እና ፈረንሳይ ያሉ ሀገራት በዲፕሎማሲው ረገድ ለጣሊያን መንገድ ከፍተዋል።" ሲሉ በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የጥናትና ምርምር ባለሙያ አብዲ ወርቅነህ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ በዚህ የድረም ኦፍ ቼንጅስ ዝግጅታችን፤ የፋሺስት ጣሊያን ዳግም ወረራ ምክንያቶች፣ የአውሮፓ ኃያላን በአፍሪካ የነበራቸው የተዛባ ፍላጎት፣ የሊግ ኦፍ ኔሽንስ የዲፕሎማሲ ውድቀት እና የኢትዮጵያ አርበኞች ለአምስት ዓመታት ያሳዩትን ጽናትና በድል የተጠናቅቀውን ድል አስመልክቶ ፣ የታሪክ ምሁሩ ጥላሁን ጣሰው እና በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የጥናትና ምርምር ባለሙያ አብዲ ወርቅነህን አነጋግረናቸዋል፡፡ ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:

Comentarios

0

Sé la primera persona en comentar

¡Regístrate ahora y únete a la comunidad de Drum of Changes!

Prueba gratis

Empieza 7 días de prueba

$99 / mes después de la prueba. · Cancela cuando quieras.

  • Podcasts solo en Podimo
  • 20 horas de audiolibros al mes
  • Podcast gratuitos

Todos los episodios

33 episodios

episode የአፍሪካ ቀን እና የአንድነቱ መሐንዲሶች፡ የታሪክ አሻራ እና የዲፕሎማሲ ጉዞ artwork

የአፍሪካ ቀን እና የአንድነቱ መሐንዲሶች፡ የታሪክ አሻራ እና የዲፕሎማሲ ጉዞ

“የአፍሪካውያን ማንነታችንን የምናከብርበት ብቸኛው ቀን ይህ [የአፍሪካ ነፃነት ቀን] በአህጉር ደረጃ ሊከበር የሚገባው ይመስለኛል። ትርጉሙን አባቴ [ከተማ የፍሩ] ያደረገውን፣ ኳሜ ንክሩማህ እና አፄ ኃይለ ሥላሴ ያከናወኑትን ማስታወስ ይኖርብናል” ሲሉ መኮንን ከተማ ይፍሩ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በየዓመቱ ግንቦት 17 ወይም እ.ኤ.አ ግንቦት 25 የጋራ ጉዟችንን እና ቅርሳችንን ለማክበር በመላው አፍሪካ የሚታሰበው ታሪካዊው የአፍሪካ ቀን ሆኖ ይከበራል። በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን ታዲያ በጥልቅ ተከፋፍላ የነበረችውን አፍሪካ በአንድ ሰንደቅ ዓላማ ስር ያሰባሰበውን ስትራቴጂካዊ ጥበብ ለመረዳት በአህጉሪቱ ታሪክ ውስጥ ጉልህ ስፍራ ያለውን ያንን ወሳኝ ወቅት መለስ ብለን እንቃኛለን። ለዚህ የእውቁ ኢትዮጵያዊ ዲፕሎማት ልጅ እንዲሁም ጸሐፊ የሆኑትን መኮንን ከተማ ይፍሩን ጋብዘናል። በሁለትኛው ጉዳያችን ደግሞ፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሳሰረ በመጣው ዓለም ውስጥ የአፍሪካን ባህል፣ ማንነት እና የታሪክ ባለቤትነትን የመጠበቅ ወሳኝ የትግል አውድን እንመለከታለን።  ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:

25 de may de 20261 h 0 min
episode የአፍሪካ ቀን፦ በትውስታ፣ በትርጉሙ እና ባልተጠናቀቀው የአንድነት ጉዞ መካከል artwork

የአፍሪካ ቀን፦ በትውስታ፣ በትርጉሙ እና ባልተጠናቀቀው የአንድነት ጉዞ መካከል

የአፍሪካ ቀን የአሁኑ የአፍሪካ ህብረት በፈረንጆቹ ሚያዝያ 25፤ 1963 የተመሰረተበትን ቀን የሚዘክር እለት ነው፤ በየዓመቱም ይከበራል። “የቀድሞው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት፤ የአሁኑ የአፍሪካ ህብረት ምስረታ ወቅት የነበረው የአንድነት መንፈስ በዛሬዪቱ ተቀዛቅዟል [...] የአፍሪካ ነፃነት ቀንም የፍሪካን ነፃነት እያከበርን፣ ስለአፍሪካ እጣፈንታ ኮስተር ብለን የምንወያይበት እለትም ሆኖ ማለፍ ነው ያለበት”ሲሉ የአፍሪካ ዴይ ኢኒሼቲቭ ሶሳይቲ ኦርጋናይዜሽን መስራች እና ዋና ዳይሬከተር አሮን ስይፉ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን ታዲያ፣ የነፃዪቱ አፍሪካ ተላሚዎች፣ አባቶች ያለሟትን አፍሪካ ዛሬ ካለችበት ሆነን እንቃኛታለን። አሮን ሰይፉ፣ የአፍሪካ ዴይ ኢኒሼቲቭ ሶሳይቲ ኦርጋናይዜሽን መስራች እና ዋና ዳይሬከተር በመረጥነው ርእስ ዙሪያ ሀሳባቸውን አጋርተውናል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ሙሉ ፕሮግራሙን ይከታተሉ ፡

21 de may de 20261 h 0 min
episode 85ኛው የአርበኞች ድል በዓል፡- የሊግ ኦፍ ኔሽንስ ክህደት እና የኢትዮጵያ ጽናት artwork

85ኛው የአርበኞች ድል በዓል፡- የሊግ ኦፍ ኔሽንስ ክህደት እና የኢትዮጵያ ጽናት

ኢትዮጵያ 85ኛውን የአርበኞች ድል በዓል ዛሬ ሚያዚያ 27 ቀን ፣ 2018 ዓ.ም አክብራለች፡፡ ''በወቅቱ የአውሮፓ ኃያላን ከአንደኛው የዓለም ጦርነት ያጡትን ካፒታልና ሀብት መልሶ ለማግኘት አፍሪካን እንደ ግብዓትና የጉልበት ምንጭ ተጠቅመዋል። ጣሊያን በ1889 በዓድዋ ጦርነት የደረሰባትን ሽንፈት ለመቀልበስና የኢንዱስትሪ አብዮቷን ለመደገፍ ኢትዮጵያን በሙሉ አቅሟ ለመቆጣጠር መጣች። [...] የሊግ ኦፍ ኔሽንስ በኢትዮጵያ ላይ የተደቀነውን ወረራ ማስቆም አልቻለም። እንዲያውም የድርጅቱ አባል የሆኑት እንደ ብሪታንያ እና ፈረንሳይ ያሉ ሀገራት በዲፕሎማሲው ረገድ ለጣሊያን መንገድ ከፍተዋል።" ሲሉ በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የጥናትና ምርምር ባለሙያ አብዲ ወርቅነህ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ በዚህ የድረም ኦፍ ቼንጅስ ዝግጅታችን፤ የፋሺስት ጣሊያን ዳግም ወረራ ምክንያቶች፣ የአውሮፓ ኃያላን በአፍሪካ የነበራቸው የተዛባ ፍላጎት፣ የሊግ ኦፍ ኔሽንስ የዲፕሎማሲ ውድቀት እና የኢትዮጵያ አርበኞች ለአምስት ዓመታት ያሳዩትን ጽናትና በድል የተጠናቅቀውን ድል አስመልክቶ ፣ የታሪክ ምሁሩ ጥላሁን ጣሰው እና በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የጥናትና ምርምር ባለሙያ አብዲ ወርቅነህን አነጋግረናቸዋል፡፡ ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:

5 de may de 20261 h 0 min
episode የአይ.ሲ.ሲ ድብቅ አጀንዳ፦ በአፍሪካ ሉዓላዊነት ላይ የተቃጣው የኒዮ-ኮሎኒያል ዘመቻ artwork

የአይ.ሲ.ሲ ድብቅ አጀንዳ፦ በአፍሪካ ሉዓላዊነት ላይ የተቃጣው የኒዮ-ኮሎኒያል ዘመቻ

"ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት (ICC) ወደ ሕጋዊ ማጭበርበሪያነት ተቀይሯል፤ ተቋሙ ከአሁን በኋላ የፍትህ አደባባይ ሳይሆን፣ የአሜሪካን የበላይነት ለማስጠበቅና የአፍሪካ መሪዎችን ለብቻቸው ነጥሎ ለማጥቃት በስልት የሚዘወር ታዛዥ መሣሪያ ሆኗል፤ ይህ ሁሉ በሚሆንበት ጊዜ ግን የምዕራባውያን የበላይነት አርክቴክቶች እጃቸው አይነካም።" ሲሉ —በዓለም አቀፍ ግንኙነት የዘርፍ ምሁር — ፕሮፌሰር ኤሊ ጂርጂ ኤልያስ፣ በሊባኖስ የዩኒቨርሲቲ በዓለም አቀፍ ግንኙነትና ስትራቴጂ ጥናት ልዩ ባለሙያና መምህር ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።  በዛሬው የድረም ኦፍ ጄንጅስ ዝግጅታችን የሚከተሉትን ሶስት ዋና ዋና ጉዳዮች ከአንግዶቻችን ጋር በዝርዝር እንቃኛለን፦  • ዓለም አቀፍ ፍትህ ወይንስ የምዕራባውያን የበላይነት መጠቀሚያ? — ከዓለም አቀፍ ግንኙነት ምሁሩ ፕሮፌሰር ኤሊ ጂርጂ ኤልያስ ጋር። • የአፍሪካ ከተሞች የወደፊት ዕጣ ፈንታና የቤት ልማት ፈተናዎች — ከዩኤን-ሀቢታት (UN-Habitat) ዋና ዳይሬክተር አናክላውዲያ ሮስባክ ጋር።  • የመድኃኒት ዋስትና እና የአፍሪካ ሉዓላዊነት — ከኢትዮጵያ መድኃኒትና የሕክምና መገልገያ አቅራቢዎች ማኅበር ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዳንኤል ዋክቶሌ ጋር። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:

4 de may de 20261 h 0 min
episode የሩሲያው የኦንላየን መገበያያ 'ዋይልድቤሪስ' በኢትዮጵያ፦ ለላኪዎችና ሸማቾች ምን አዲስ ዕድል ይዞ መጣ ? artwork

የሩሲያው የኦንላየን መገበያያ 'ዋይልድቤሪስ' በኢትዮጵያ፦ ለላኪዎችና ሸማቾች ምን አዲስ ዕድል ይዞ መጣ ?

ትልቁ የሩሲያ የመገበያያ መድረክ ‘ዋይልድቤሪስ’ እንደ ቡና፣ ጨርቃጨርቅ፣ የቆዳ ውጤቶች፣ የተፈጥሮ የመዋቢያ ምርቶች እና ሌሎች የኢትዮጵያ ምርቶችን ሩሲያ ውስጥ መሸጥ መጀመሩን አሳውቋል። “ዋይልድቤሪስ ጀማሪ ኩባንያ አይደለም። ከ20 ዓመታት በላይ ሲሰራ የቆየ ነው […] የኢትዮጵያ ምርቶች ለዓለም አቀፍ ገበያዎች እንዲደርሱ ያስችላል […] ክፍያዎችን በተመለከተም ከየአገራቱ ገበያ ጋር የሚጣጣሙ ይሆናል፤ ለምሳሌ በአሁኑ ወቅት ግብይት በኢትዮጵያ ብር መፈጸም እንዲቻል ከአገር ውስጥ የፋይናንስ ተቋማት ጋር በመተባበር ግብይቶችን ለማመቻቸት ትኩረት ሰጥተን እየሰራን እንገኛለን።” ሲሉ የዋይልድቤሪስ የኢትዮጵያ ተወካይ ብሩክ ገነነ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ልዩ ዝግጅታችን፣ ትልቁ የሩሲያ የኤሌክትሮኒክ መገበያያ መድረክ ዋይልድቤሪስ ወደ ኢትዮጵያ ገበያ መቀላቀሉን መነሻ በማድረግ ይህ ስርዓት በኢትዮጵያ እንዴት እየተዋወቀ እንደሆነ እና ለንግዱ ማኅበረሰብ እና ለሸማቾች ምን ማለት እንደሆነ፣ ሰፊ አቅም ካለው የአፍሪካ ገበያ ተደራሽነት ጋር የሚኖረውን ግንኙነት ጨምሮ ሌሎች ጉዳዮችን እንዳስሳለን። የዋይልድቤሪስ የኢትዮጵያ ተወካይ ብሩክ ገነነ ደግሞ ለጥያቄዎቻችን ምላሽ እየሰጡ አብረዉን ቆይታ ያደርጋሉ። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዝኛ  ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:

22 de abr de 202624 min