Continental Drift
የአፍሪካ ሉዓላዊነት ጥያቄ ከማዕድን እና ከንግድ ኮሪደሮች ባለፈ፣ አህጉሪቱን የሚያስተዳድሩ መሪዎች በሚቀረጹበት የዕውቀት ሥርዓት ላይ ያተኩራል። በሌላ በኩል ደግሞ አዲስ አበባ የመጀመሪያውን አህጉራዊ የተራራ ብስክሌት ውድድር በማስተናገድ፣ ከተማን እንደ ዲፕሎማሲ እና የ'ሶፍት ፓወርን' መድረክነት እየተጠቀመችበት ትገኛለች። "አፍሪካውያን የራሳቸውን ሥርዓተ-ትምህርት ማዘጋጀት አለባቸው። ይህም በጣም አስፈላጊ ነው። ሌላው ችግር በመካከላችን ጠንካራ አህጉራዊ ግንኙነት የለንም። ስለዚህ ይህንን ግንኙነት መገንባት አለብን። ይህ ጉባኤ የአፍሪካ ቢዝነስ ትምህርት ቤቶች በራሳቸው ችግሮች ላይ ተመሥርተው በጋራ እንዲሠሩ በማድረግ ረገድ ትልቅ ፋይዳ ይኖረዋል።" ሲሉ ደሳለኝ መኩሪያ ንጉሤ፣ የክቡር ኮሌጅ ፕሬዝዳንት ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ በዛሬው የኮንቲነንታል ድሪፍት ዝግጅታችን፣ አፍሪካ የራሷን ተቋማት በራሷ ፍላጎት ላይ ተመሥርታ የመገንባት ስትራቴጂን ከሁለት እንግዶች ጋር እንፈትሻለን፦ ከክቡር ኮሌጅ ፕሬዝዳንት ደሳለኝ መኩሪያ ንጉሤ ጋር ስለ ቢዝነስ ትምህርት፣ አመራር እና ስለ ዕውቀት ሉዓላዊነት፤ ከኢትዮጵያ ብስክሌት ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ወዲሙ ኃይሌ ጋር ስለ ከተማ ስፖርት ዲፕሎማሲ እና ስለ አዲስ አበባ ገጽታ ግንባታ እንወያያለን። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በአእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ ፡
21 episodios
Comentarios
0Sé la primera persona en comentar
¡Regístrate ahora y forma parte de la comunidad de Continental Drift!